ጅማ አባ ጅፋር ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት ሊጀምር ነው

ጅማ አባ ጅፋሮች የ2013 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅታቸውን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊጀምሩ ነው።

ምንም እንኳን እስካሁን ከፊፋ እግድ ጋር ተያይዞ ጅማ አባ ጅፋር በግልፅ ቡድኑን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በይፋ እንዳስፈረሙ ማረጋገጫ ባይገኝም ወደ ቡድኑ እንዲካተቱ የታሰቡ አዳዲስ ተጫዋቾች እና ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ ከነገ ጀምሮ ሁሉም የቡድኑ አባላት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ጨምሮ የኮቪድ ፕሮቶኮል በሚያዘው መሠረት ምርመራ አድርገው በቀጣይ ቀናት ዝግጅት ለመጀመር ነገ ጅማ ከተማ እንደሚገቡ ለማረጋገጥ ችለናል።

የክለቡ የቦርድ አመራር ከክለቡ ጋር ተያይዞ ዓምና በይደር የቆዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሥራ እየሰሩ እንደሚገኝና በቅርቡም ክለቡ በሙሉ አቅሙ ተጠናክሮ ወደ ውድድር ለመግባት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ሰምተናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!