​ሰበታ ከተማ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቧል

ሰበታ ከተማ ከነገ ጀምሮ ወደ ዝግጅት ይገባል፡፡

ከቀናት በፊት ዘግየት ብሎ ያወጣውን የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን በመተው ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱን በይፋዊ የፊርማ ሥነ ስርዓት የሾመው ሰበታ ከተማ ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት በአዲሱ አሰልጣኝ መሪነት ማድረግ ይጀምራል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም ተጫዋቾች ወደ ካምፕ መግባት የሚጀምሩ ሲሆን ነገ (ሐሙስ) የኮቪድ 19 ምርመራ ለአጠቃላይ የክለቡ አካላት ይደረግና ውጤቱን መሠረት በማድረግ የፊታችን ቅዳሜ ሰበታ ከተማ ስታዲየም ላይ ልምምድ እንደሚጀምር አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ክለቡ የፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታውን ፋሲል ከነማን በመግጠም የሚጀምር ይሆናል፡፡
©ሶከር ኢትዮጵያ