ወላይታ ድቻ 2-0 አዳማ ከተማ
24′ መሳይ አንጪሶ
85′ ዮሴፍ ዴንጌቶ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በወላይታ ድቻ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ አዳማ ከተማ የውድድር ዘመኑን 2ኛ ሽንፈት አስተናግዶ ሊጉን የመምራት እድሉን አምክኗል፡፡ ወላይታ ድቻ ደግሞ ወደ 6ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4ኛ ዳኛው ተጨማሪ 4 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡
ስንታየሁ መንግስቱ ገብቶ አላዛር ፋሲካ ወጥቷል
85′ ዮሴፍ ዴንጌቶ በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኘውን ኳስ መሬት ለመሬት መትቶ የድቻን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
አዳማ ከተማ ቡልቻ ሹራ ገብቶ እሸቱ መና ወጥቷል
ወላይታ ድቻ ተክሉ ታፈሰ ገብቶ ሙባረክ ሽኩሪ ወጥቷል
77′ የቀድሞ ክለቡን በአዳማ ማልያ ለመጀመርያ ጊዜ እየገጠመ የሚገኘው እሸቱ መና ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ሞክሮ ጃኮብ ይዞበታል፡፡
67′ ወደ አዳማ የግብ ክልል በረጅሙ የተላከውን ኳስ በግብ ጠባቂው ጃኮብ ስህተት ወደ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚነት ቢቀየርም አላዛር ሳጠቀምበት ቀርቷል፡፡ አሰልጣን መሳይ ተፈሪ የድቻ ደጋፊዎች ቡድናቸውን እንዲያበረታቱ በማነሳሳት ላይ ይገኛል፡፡
አዳማ ከተማ ዮናታን ከበደ ወጥቶ ጫላ ድሪባ ገብቷል
ወላይታ ድቻ ፀጋዬ ብርሃኑ ወጥቶ ፀጋ አለማየሁ ገብቷል
63′ ሚካኤል ጆርጅ በዮሴፍ ዴንጌቶ ላይ ከባድ ፋውል ሰርቷል በሚል በቀጥታ የቀይ ካርድ ተመልክቷል፡፡ አሁን ከሁለቱም አንድ አንድ ተጫዋች ወጥቷል፡፡
52′ ግቡን ያስቆጠረው መሳይ አንጪሶ በማዕዘን ምት ሽሚያ ወቅት ጥፋት ሰርተሃል በሚል በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡ ወላይታ ድቻዎች ውሳኔውን ባለመቀበል ክስ አስመዝግበዋል፡፡ ጨዋታው አሁን ውጥረት እየነገሰበት ይገኛል፡፡
51′ አዳማዎች በተከታታይ 4ኛ የማእዘን ምታቸውን አግኝተዋል፡፡ ቀይ ለባሾቹ የአቻነት ጎል ለማግኘት ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡
47′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ዮናታን ከበደ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡ አስደንጋጭ የግብ ሙከራ ነበር፡፡
ደሳለኝ ደባሽ ገብቶ ፋሲካ አስፋው ወጥቷል፡፡
የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቀቀ
ወላይታ ድቻ በግሩም ደጋፊ እና በመሳይ አንጪሶ ጎል ታግዘው የመጀመርያውን አጋማሽ 1-0 እየመሩ እረፍት ወጥተዋል፡፡
45′ የመጀመረያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 4ኛው ዳኛ ተጨማሪ 4 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡
30′ አዳማ ከተማ የጨዋታውን የመጀመርያ የግብ ሙከራ አድርጓል፡፡ ታከለ አለማየሁ ከመስመር ያሻማውን ኳስ ሻኪሩ በግንባሩ ገጭቶ የግቡን አግዳሚ ታኮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
24′ መሳይ ማልያውን አውልቆ ደስታውን በመግለጹ የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
24′ መሳይ አንጪሶ በግምት ከ20 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታው ኳስ በጃኮብ ፔንዛ መረብ ላይ አርፏል፡፡ መሳይ ማልያውን አውልቆ በመጨፈር ላይ ይገኛል፡፡ ግሩም ግብ!!!
21′ አናጋው ባደግ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ አላዛር በግንባሩ ገጭቶ ወደ ግብ ቢሞክርም ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
20′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡ አናጋው ከሞከረው ሙከራ ውጪ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ጥሩ የግብ ማግባት እንቅስቃሴ አልታየም፡፡ ከወላይታ ድቻ በኩል በድሉ መርድ መልካም እቅስቃሴ እያሳየ ነው፡፡
13‘ ወንድወሰን የህክምና እርድታ ተደርጎለት ወደ ጨዋታው ተመልሷል፡፡ ጨዋታውም ለ3 ደቂቃ ተስተጓጉሎ አሁን ተጀምሯል፡፡
9′ ወንድወሰን አሸናፊ ከሚካኤል ጆርጅ ጋር ተጋጭቶ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ የህክምና እርዳታ እየተደረገለትም ይገኛል፡፡ ምናልባትም የወላይታ ድቻ የመጀመርያ የተጫዋች ቅያሪ ሊፈፀም ይችላል፡፡
7′ አናጋው ባደግ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ ጃኮብ ፔንዛ አድኖበታል፡፡
08:55 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች በማማሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
ወንድወሰን አሸናፊ
አናጋው ባደግ – ሙባረክ ሽኩሪ – ቶማስ ስምረቱ – ፈቱዲን ጀማል
አማኑኤል ተሾመ – ዮሴፍ ደንጌቶ – በድሉ መርዕድ – ፀጋዬ ብርሃኑ – መሳይ አንጪሶ
አላዛር ፋሲካ
የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
ጃኮብ ፔንዛ
እሸቱ መና – ወንድወሰን ሚልኪያስ – ሞገስ ታደሰ – ተስፋዬ በቀለ
ዮናታን ከበደ – ፋሲካ አስፋው – ታከለ አለማየሁ
ሚካኤል ጆርጅ – ታፈሰ ተስፋዬ – አቢኮዬ ሻኪሩ