​የዐፄዎቹ ወሳኝ ተጫዋች ጉዳት አጋጥሞታል

በካፍ ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ በመሆናቸው በአዲስ አበባ ዝግጅት እያደረጉ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች ወሳኝ ተጫዋቻቸው ጉዳት አጋጥሞታል።

በዘንድሮ ዓመት በካፍ ኮፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ፋሲል ከነማ ከቱኒዚያው ዩ ኤስ ሞናስቲር ጋር መደልደሉ ይታወቃል። ለዚህም ጨዋታ በማሰብ ከቀናት በፊት መቀመጫውን አዲስ አበባ በማድረግ ሲኤምሲ በሚገኘው የንግድ ባንክ ሜዳ ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዛሬው የረፋድ ላይ ለሁለት ተከፍለው ባደረጉት የሙሉ ሜዳ ጨዋታ እንቅስቃሴ ወቅት የ2011 ኮከብ እና የዐፄዎቹ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ሱራፌል ዳኛቸው ጉዳት አሰተናግዶ ልምምድ አቋርጦ ወጥቷል።

የጉዳቱ ሁኔታ የግራ እግሩ የውስጥ እግር ቅጥቅጥ እንደሆነ በህክምና ባለሙያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ጉዳቱ ብዙም የከፋ እንዳልሆነና በቀጣዮቹ ቀናት ወደ መደበኛ ልምምዱ እንደሚመለስ ሰምተናል። 

የቡድኑ ዝግጅት እና የጉዞ ሁኔታ አስመልክቶ ከሰዓታት በኃላ ሰፊ ዘገባ ይዘን የምንመለስ መሆኑን ከወዲሁ መግለፅ እንፈልጋለን።

©ሶከር ኢትዮጵያ