ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምሳ ግብዣ ተደረገለት

በትናንትናው ዕለት በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ኒጅርን ከጨዋታ ብልጫ ጋር ያሸነፈው ብሔራዊ ቡድኑ የማበረታቻ ሽልማት እና የምሳ ግብዣ ተደረገለት።

ቡድኑ ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን እና ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተቀናጀ ሁኔታ ዛሬ ረፋድ ላይ በአያት ሪጀንሲ ሆቴል የምሳ ግብዣ የማበረታቻ ሽልማት እየተደረገለት ነው። በፕሮግራሙ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል ።

በሽልማቱ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ባይወጣም ለብሔራዊ ቡድኑ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ሊበረከትለት እንደሚችል ሰምተናል።

©ሶከር ኢትዮጵያ