አፍሪካ | የካፍ ፕሬዝዳንት ታግደዋል

የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ የሆነውን ካፍ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት አህመድ አህመድ የአምስት እግድ በፊፋ ተላልፎባቸዋል።

ማዳጋስካራዊው የ60 ዓመት ግለሰብ ከ2017 ጀምሮ የአፍሪካን እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ ቆይቷል። ከሳምንታት በፊትም የኮቪድ-19 ቫይረስ ተጠቂ እንደነበሩ ይታወሳል። አሁን በሰበር ዜና በወጣ መረጃ መሠረት ደግሞ የዓለም የእግርኳስ የበላይ የሆነው ፊፋ ግለሰቡን ለአምስት ዓመታት ማገዱ ተገልጿል።

እየወጡ ባሉ ዘገባዎች መሠረት ግለሰቡ በርካታ የመተዳደሪያ ደንቦችን (codes of ethics) በመጣሳቸው እግዱ እንደተላለፈባቸው ያመላክታሉ። ከምንም በላይ ደግሞ ከታማኝነት ጋር የተያያዙ እና ከጥቅም ጋር የተያያዙ ደንቦችን መጣሳቸው እንደ ዋነኛ ምክንያትነት እየተገለፀ ይገኛል።

አዲስ ነገሮች እስካልተፈጠሩ ድረስ አህመድ አህመድ በመጋቢት ወር ከሚካሄደው የካፍ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫም ውጪ እንደሚሆኑም ተዘግቧል።

© ሶከር ኢትዮጵያ