ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ንግድ ባንክ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ ለ2013 ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበትም ቀን ታውቋል።

የሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሳምንታት በፊት የ10 ነባር ተጫዋቾችን ውል ማደሱ ይታወሳል። ክለቡ የነባር ተጫዋቾችን ውል ከማደሱ በተጨማሪ ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ፣ ሰናይት ቦጋለ እና አያንቱ ቶሎሳን ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ታህሳስ 10 ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን ውድድር በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ስብስቡም ከቀናት በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ በማከናወን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ለመጀመር እየተሰናዳ ይገኛል። በመጪው እሁድም (ኅዳር 13) ቡድኑ ወደ ሀዋሳ በመጓዝ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።

በተያያዘ ዜና አራት ወሳኝ ተጫዋቾችን ቀደም ብሎ ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ባንክ ትዕግስት ኃይሌን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ማስፈረሙ ተረጋግጧል። ከኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ተገኝታ ለአራት ዓመታት በአካዳሚው ቆይታን ያደረገችው ትዕግስት ከዛም ጉዞዋን ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማድረግ ግልጋሎት ስትሰጥ ቆይታለች። ዘንድሮ ደግሞ የመሐል ተከላካዩዋ የአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛውን ስብስብ በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሏ ተነግሯል።

©ሶከር ኢትዮጵያ