ከፍተኛ ሊግ | ኮልፌ ቀራኒዮ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሐ ምድብ ስር ከተደለደሉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአሰልጣኝ መሐመድ ኑርንማን ውል ሲያራዝም አስራ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡

ግብ ጠባቂዎች፡- አዲሱ ቦቄ (ከየካ)፣ ሃይማኖት አዲሱ (ከሱሉልታ) 

ተከላካዮች፡- አዳነ አሰፋ (ከአዲስ አበባ ፖሊስ)፣ ሀብታሙ ጪማ (ከዳሞት ከተማ)፣ መላኩ ተረፈ (ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ)፣ አቡበከር ካሚል (ከኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ዳዊት ቹቹ (ከባቱ ከተማ)፣ ቃልአብ ኪዱ (ከሶሎዳ ዓድዋ)

አማካዮች፡- ሙሉቀን አሰፋ (ከቤንች ማጂቡና)፣ አቡበከር ሻሚል (ከአዲስከተማ ክፍለከተማ)፣ ሙሉዓለም በየነ (ከአክሱም)፣ ኪሩቤል ወንድሙ (ከቂርቆስ)፣ አብዱልቃድር ቀድሩ (ከሱሉልታ) 

አጥቂዎች፡- ሮቤል ጥላሁን (ከአቃቂ ቃሊቲ)፣ ኤርሚያስ ዳንኤል (ከሻሸመኔ ከተማ)
ውላቸው የተራዘሙ 

አዲስኪዳን ኪዳነማርያም (ግብጠባቂ)፣ አህመድ ሰዒድ (ተከላካይ)፣ አበራ ታደሰ (ተከላካይ)፣ ፈቱ አብደላ (አማካይ)፣ ደሳለኝ ወርቁ (አማካይ)፣ ሀይከር ደዋሙ (አጥቂ)፣ አንዋር ዱላ (አጥቂ) ብሩክ ሙሉጌታ (አጥቂ)

© ሶከር ኢትዮጵያ