ከፍተኛ ሊግ | ኢኮሥኮ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ከሳምንታት በፊት አስፈርሞ የነበረው ኢኮሥኮ ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያምን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው የምድብ ለ ተወዳዳሪዌ ኢኮሥኮ ከሳምንት በፊት በርካታ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን አሁንም ተጨማሪ አራት ተጫዋቾች ከተለያዩ ክለቦች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ የራስወርቅ ተረፈ (ግብ ጠባቂ ከአክሱም)፣ ይገርማል መኳንንት (ግብ ጠባቂ ከአውስኮድ)፣ መላኩ ተፈራ (ተከላካይ ከአውስኮድ) እና ፍፁም ግርማ (አማካይ ከወልቂጤ) አዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ