ሰበታ ከተማ ተከላካይ አስፈረመ

የመሀል እና የመስመር ተከላካዩ ቢያድግልኝ ኤልያስ ሰበታ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከ31 ዓመታት በኋላ በተሳተፈችበት የ2013 አፍሪካ ዋንጫ ላይ ከነበሩ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ቢያድግልኝ በሲዳማ ቡና ያሳየውን ድንቅ አቋም ተከትሎ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማምራት ጥሩ ጊዜ በክለቡ አሳልፏል። ከፈረሰኞቹ ጋር በ2008 ከተለያየ በኋላም በአርባምንጭ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ወልዲያ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በመቐለ 70 እንደርታ በመጫወት አሳልፏል፡፡ “ሰበታ ከተማን በመቀላቀሌ ደስ ብሎኛል። በምወደው አሰልጣኝ የመሰልጠን ዕድሉን በማግኘቴም ውስጤ ደስታ ተፈጥሯል፡፡ በሚኖረኝ ቆይታ ጥሩ ነገሮችን አሳያለሁ ብዬ አስባለሁ።” በማለትም አስተያየቱን በአጭሩ አጋርቶናል፡፡

ሰበታ ከተማ ከቢያድግልኝ በፊት ምንተስኖት አሎ፣ ሙሉቀን ደሳለኝ፣ መሳይ ጳውሎስ፣ ዳንኤል ኃይሉ፣ ዱሬሳ ሹቢሳ፣ ቡልቻ ሹራ፣ ፍአድ ፈረጃ እና እስራኤል እሸቱን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ