ዓምና በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ የቀረው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ተካሂዶ አዲስ አመራሮችን መርጧል።
ከጠዋቱ 03:00 ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል በተካሄደው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2012 ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በርከት ያሉ አከራካሪ ጉዳዮች በተነሱ ሲሆን ዓመታዊ ሪፖርት፣ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ እና በቀጣይ የሚሻሻሉ መተዳደርያ ደንቦች እና እቅዶች ከተወያየ በኃላ በመጨረሻ ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝደንት እና በሥራ አስፈፃሚነት የሚመሩ አመራሮችን ምርጫ አካሂዷል።
በዚህ መሠረት ኃይለየሱስ ፍስሀ (ኢ/ር) ፕሬዝደንት እንዲሆኑ ሲመረጡ በሥራ አስፈፃሚነት ደግሞ አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ(ምክትል ፕሬዝደንት)፣ አማረ አንዷለም፣ አቶ ደረጄ አረጋ፣ አቶ ዘሪሁን ገብሬ፣ አቶ አንተነህ ተመስገን፣ አቶ ደመላሽ ደለለኝ፣ አቶ ይገርማል ንጉሴ (አቃቢ ነዋይ) እና አቶ ንብረት ኃይሌ በመሆን ተመርጠዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ