​በከፍተኛ ሊጉ ሦስት ምድቦች የተደለደሉ ክለቦች ታውቀዋል

የከፍተኛ ሊግ ዓመታዊ ስብሰባ እና የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በሦስቱ ምድቦች የሚገኙ ክለቦችም ታውቀዋል።

በተሰረዘው የውድድር ዓመት ከነበረው የምድብ ድልድል አንድ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ምድብ ለ ላይ የነበረው መከላከያ ወደ ምድብ ሀ፣ በምድብ ሀ የነበረው አቃቂ ቃሊቲ ደግሞ በምድብ ለ ተደልድለዋል። ይህን ተከትሎ በአቃቂ ቃሊቲ በኩል ተቃውሞ የቀረበ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና ከፍተማ ሊጉ ኮሚቴ ምላሽ ተሰጥቶበታል። 

በተጨማሪም በአንድ ቦታ ውድድሩ ስለሚካሄድ በድጋሚ ሙሉ ድልድል ይካሄድ የሚል ሀሳብ ተነስቶ በመጨረሻ “አዲስ ድልድል” ወይም “በቀደመው ድልድል” መሠረት ይካሄድ የሚሉ አማራጮች ቀርበው የቀደመው ድልድል ይቀጥል የሚለው በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።


ምድብ አንድ

ደደቢት 

ፌዴራል ፖሊስ 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ

መከላከያ

ገላን ከተማ

ሶሎዳ ዓድዋ

ደሴ ከተማ

ለገጣፎ ለገዳዲ

ወልዲያ

ወሎ ኮምቦልቻ

አክሱም ከተማ

ሰ/ሸ ደብረብርሀን

ምድብ ሁለት 

አቃቂ ቃሊቲ

ኢኮሥኮ

ነቀምቴ ከተማ

ጅማ አባ ቡና

ሻሸመኔ ከተማ

ቤንችማጂ ቡና

ጋሞ ጨንቻ

አዲስ አበባ ከተማ

ካፋ ቡና

ወላይታ ሶዶ ከተማ

ሀላባ ከተማ

ሀምበሪቾ ዱራሜ

ምድብ ሦስት

ደቡብ ፖሊስ

ቂርቆስ 

ዲላ ከተማ

ኢትዮጵያ መድን

ባቱ ከተማ

ከምባታ ሺንሺቾ

አርባምንጭ ከተማ

ኮልፌ ቀራኒዮ

ስልጤ ወራቤ

ነጌሌ አርሲ

ቡታጅራ ከተማ

የካ

©ሶከር ኢትዮጵያ