​ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ| ፋሲል ከነማዎች ቱኒዚያ ደርሰዋል 

በኮንፌደሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲርን ከሜዳ ውጭ የሚገጥመው ፋሲል ከነማ ቱኒዝያ ገብቷል ።

ዐፄዎቹ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቀጥታ ወደ ቱኒዚያ የአየር በረራ ባለመኖሩ ቀደም ብለው በማመቻቸት ሊገሸዙ ችለዋል። ትናንት ምሽት ወደ ቱኒዚያ ጉዞ የጀመሩት የቡድኑ አባላትም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስተው ወደ ግብፅ ያመሩ ሲሆን ግብፅ ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ከደረሱ በኋላ በዛው አድረው ጠዋት ወደ ቱኒዚያ አምርተዋል። በዚህም ቀን 6:45 ቱኒስ የደረሱ ሲሆን ከሁለት ሰዓት በላይ ተጉዘው ጨዋታው የሚደረግበት ሞናሲቲር ደርሰዋል። መቀመጫቸውንም ስካኔ ሆቴል አድርገዋል።
ቡድኑ ዛሬ ልምምድ ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም አድካሚ ጉዞ ከማድረጋቸው የተነሳ ነገ ጠዋት  የመጀመሪያ ልምምዳቸውን የሚያደርጉ ሲሆን በአጠቃላይ በስፍራው 19 ተጫዋቾች፣ ስድስት የአሰልጣኞች አባላት፣ አራት የቦርድ አባላት እና የህዝብ ግንኙነቱን በቱኒዚያ ይገኛሉ ።
ወደ ቱኒዚያ ያመሩት ተጫዋቾች 
ግብ ጠባቂዎች
ሚኬል ሳማኬ፣ ቴዎድሮስ ጌትነት፣ ይድነቃቸው ኪዳኔ
ተከላካዮች
ያሬድ ባየ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ እንየው ካሳሁን፣ ሰዒድ ሀሰን፣ ከድር ኩሊባሊ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ  
አማካዮች
ሀብታሙ ተከስተ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮ፣ ይሁን እንደሻው፣ ኪሩቤል ኃይሉ
አጥቂዎች 
ሽመክት ጉግሳ፣ በረከት ደስታ፣ ዓለምብርሃን ይግዛው፣ ሙጅብ ቃሲም፣ ፍቃዱ ዓለሙ
©ሶከር ኢትዮጵያ