​ሴካፋ U-20 | ኢትዮጵያ የውድድሩ የመጀመርያ ድሏን አስመዘገበች

በታንዛኒያ እየተከናወነ በሚገኘው የሴካፋ ከ 20 ዓመት ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከሃያ ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛ የምድብ ጨዋታው ሱዳንን ከመመራት ተነስቶ አሸንፏል።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ባለፈው ሰኞ በኬንያ 3-0 ከተሸነፈው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ተመስገን በጅሮንድ እና በየነ ባንጃን በ በእያሱ ለገሰ እና እዮብ ዓለማየሁ ምትክ አሰልፈዋል። 

በጨዋታው ሱዳኖች አብዱልከሪም ዩስፍ በ32 እና 45ኛዎ ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች የመጀመርያውን አጋማሽ 2-0 እየመሩ ያጠናቀቁ ሲሆን ከዕረፍት በኋላ ተሻሽለው የገቡት ኢትዮጵያዎች 58ኛው ደቂቃ በየነ ባንጃ ባስቆጠረው ጌሩም ጎል ልዩነቱን ሲያጠቡ ብሩክ በየነ በ72ኛው (ፍፁም ቅጣት ምት) እና 79ኛው ደቂቃ (በጨዋታ) አከታትሎ ባስቆጠራቸው ጎሎች ተመሪነቱን በመቀልበስ የ 3-2 ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

(Edited..)

የምድቡ ጨዋታዎች

ሰኞ ኅዳር 14

ኢትዮጵያ 0-3 ኬንያ 

ረቡዕ ኅዳር 16

ሱዳን 2-3 ኢትዮጵያ

ዓርብ ኅዳር 18

ኬንያ ከ ሱዳን

© ሶከር ኢትዮጵያ