​ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በዚህ ሳምንት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታን ይመራሉ

የፊታችን ዕሁድ የሚደረገውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመራል፡፡

የ2020/21 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በዚህ ሳምንት በሚደረጉ ጨዋታዎች በይፋ ይጀመራል፡፡ ከእነኚህ ጨዋታዎች መካከል ቦትስዋና ጋቦሮኒ  ላይ የፊታችን ዕሁድ ከቀኑ 10፡30 በናሽናል ስታዲየም ኦራፖ ዩናይትድ በሜዳው የሩዋንዳውን ስፖርቲቭ ኪጋሊን የሚያስተናግድ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ጨዋታውን ይመሩታል፡፡ ኃይለየሱስ ባዘዘው ወደ ኢንተርናሽናል ዳኝነት ከተመለሰ በኃላ በመሐል ዳኝነት ጨዋታውን በመምራት ዳግም በአፍሪካ መድረክ ብቅ የሚል ሲሆን አብረውት የአፍሪካ መድረክ ባለ ልምዱ ክንዴ ሙሴ እና ሸዋንግዛው ተባበል በረዳት ዳኝነት አማኑኤል ኃይለስላሴ በአራተኛ ዳኝነት ይህን ጨዋታ እንደሚመሩ ካፍ ገልጿል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ