​ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ዱራሜ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀምበሪቾ ዱራሜ አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠረ በኃላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስብ አካቷል፡፡

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር በሀድያ ሆሳዕና እና ደቡብ ፖሊስ አብሮ መስራት የቻለው ግብ ጠባቂው ሀብቴ ከድር (ከሀዋሳ ከተማ) እንዲሁም በተመሳሳይ በደቡብ ፖሊስ ከአሰልጣኙ ጋር አብሮ የሰራው የመስመር አጥቂው ብሩክ ኤልያስ ከአምስት አመት በኃላ ቢጫ ለባሾቹን ለቆ ሀምበሪቾን ተቀላቅሏል፡፡ ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ከዛም በፋሲል ከነማ የተጫወተው አማካዩ ፀጋአብ ዮሴፍ፣ ንስሀ ታፈሰ (ከአክሱም / አማካይ) አቦነህ ገነቱ (ከአርባምንጭ / አማካይ) እንዲሁም ሀላባ ከተማን እንደተቀላቀለ በአሰልጣኝ ደረጀ በላይ ተገልፆ የነበረው አጥቂው ዳንኤል ዳዊት ሀምበሪቾን ተቀላቅሎ በፌዴሬሽን መፅደቁን የክለቡ ተወካይ አቶ ጌዲዮን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ክለቡ የ2013 የውድድር ዘመን ዝግጅቱን አዳዲሶቹን እና ነባሮችን በመያዝ በቀጣዩ ሳምንት ልምምድ እንደሚጀምርም የላከልን መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ