የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን ስብሰባ እና የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ተከናውኗል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የተከፈተው የዛሬው መርሐ ግብር በፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣ በአንደኛ ሊግ ኮሚቴ አቶ ስንታየሁ እና አቶ የሺዋስ እንዲሁም በውድድር ባለሙያ አቶ ከበደ ወርቁ የተመራ ሲሆን በውድድሩ ደንብ፣ የውድድር ቦታዎች፣ የውድድር አካሄድ፣ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል፣ ከዳኝነት ህጎች እና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበት ለተነሱ ጥያቄዎች ከስብሰባው መሪዎች እና ከፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴ አባል ዶ/ር ቃልኪዳን ዘገየ እንዲሁም በዳኞች ማኅበር ም/ሰብሳቢ ሚካኤል አርዓያ ገለፃ ተሰጥቶባቸዋል።
በዛሬው ስብሰባ ውሳኔ የተሰጡባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው።
– የውድድር መጀመርያ ከዚህ ቀደም ከተገለፀው ታኅሣሥ 11 በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ታኅሣሥ 18 ተሸጋግሯች። ተያይዞም ክለቦች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ እስከ ታኅሣሥ 12 ድረስ እንዲያጠናቅቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
– የውድድር ሜዳዎች የተመረጡት የኮቪድን ፕሮቶኮል ከሚያሟሉ 17 ሜዳዎች መካከል ከሌሎቹ ሊጎች መርሐ ግብር ባማከለ መልኩ እንደሆነ ተገልጿል።
– ውድድሩ እየተካሄደ በአስገዳጅ ሁኔታዎች ምክንያት መቀጠል ካልተቻለና ከ 50+1 በመቶ በላይ ጨዋታዎች ከተከናወኑ እንደተጠናቀቀ ተቆጥሮ በመጨረሻ ውጤትነት ይፀድቃል።
– የማጠቃለያ ውድድር ከዙሩ መጠናቀቅ በኋላ የሚከናወን ሲሆን 18 ክለቦች እንደሚካፈሉ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ከየምድቡ ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ክለቦች ወደ ማጠቃለያ ዙር በቀጥታ የሚያልፉበት አሰራር ቀርቶ የየምድቡ ተሳታፊ ቡድኖች መጠን ታሳቢ በማድረግ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል። በዚህም መሠረት ከአምስት – ሰባት ተሳታፊ ካለው ምድብ ሁለት፣ ከስምንት እስከ አስር ተሳታፊ ካለው ምድብ ሦስት እንዲሁም ከአስር በላይ ተሳታፊ ካለው ምድብ አራት ቡድኖች ወደ ማጠቃለያው የሚሸጋገሩ ይሆናል።
– በየምድባቸው የመጨረሻ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች ወደ ክልሎቻቸው ወርደው ይወዳደራሉ።
ምድብ አንድ
ኤጀሬ ከተማ፣ ወሊሶ ከተማ፣ አምቦ ከተማ፣ ሆለታ ከተማ፣ መቱ ከተማ፣ ቡራዩ ከተማ፣ ንስር ክለብ፣ አሶሳ ከተማ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – አሰላ | 2ኛ ዙር – ሰበታ
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – ሦስት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
ቡራዩ ከ ወሊሶ
አምቦ ከ ሆለታ
መቱ ከ ኤጀሬ
አሶሳ ከ ንስር
ምድብ ሁለት
ሞጆ ከተማ፣ መተሐራ ስኳር፣ መቂ ከተማ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ፣ ሐረር ከተማ፣ ገደብ ሀሳሳ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ ሱሉልታ ከተማ፣ አራዳ ክ/ከተማ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – ቢሾፍቱ | 2ኛ ዙር – አሰላ
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – ሦስት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
ቢሾፍቱ ከተማ ከ መተሐራ ስኳር
ሞጆ ከተማ ከ መቂ ከተማ
ወንጂ ስኳር ከ ገደብ ሀሳሳ
አራዳ ክ/ከተማ ከ ሐረር ከተማ
ሱሉልታ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ
ምድብ ሦስት
አማራ ፖሊስ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ደባርቅ ከተማ፣ እንጅባራ ከተማ፣ ላሶታ ላሊበላ፣ ዳሞት ከተማ፣ የጁፍሬ ወልዲያ፣ መርሳ ከተማ፣ ጎጃም ደብረማርቆስ፣ ዳንግላ ከተማ፣ አማራ ውሃ ሥራ፣ ደጋን ከተማ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – ደብረማርቆስ | 2ኛ ዙር – ባህር ዳር
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – አራት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
እንጅባራ ከ ደጋን ከተማ
ጎጃም ደ/ማርቆስ ከ ዳንግላ ከተማ
የጁ ፍሬ ከ ደባርቅ ከተማ
ዳሞት ከተማ ከ አምባ ጊዮርጊስ
አማራ ፖሊስ ከ ላስታ ላሊበላ
አማራ ውሃ ሥራ ከ መርሳ ከተማ
ምድብ አራት
ልደታ ክ/ከተማ፣ ጉለሌ ክ/ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ክ/ከተማ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ቦሌ ገርጂ ማኅበረሰብ፣ የቄራ አንበሳ፣ ለገጣፎ 01፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ መከላከያ ቢ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – ሰበታ | 2ኛ ዙር – ቢሾፍቱ
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – ሦስት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
ቄራ አንበሳ ከ አአ ፖሊስ
አዲስ ከተማ ከ ልደታ
ንፋስ ስልክ ከ ሰንዳፋ በኬ
ጉለሌ ከ ቦሌ ገርጂ
ለገጣፎ 01 ከ መከላከያ
ምድብ አምስት
ሀውዜን ከተማ፣ ትግሬይ ዋልታ ፖሊስ፣ ፈራውን ከተማ፣ ትግራይ ውሃ ሥራ፣ ራያ አዘቦ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – መቐለ | 2ኛ ዙር – ዓዲግራት
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – ሁለት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
ራያ አዘቦ ከ ትግራይ ውሃ ሥራ
ሐውዜን ከተማ ከ ትግራይ ዋልታ
አራፊ – ፈራውን ከተማ
ምድብ ስድስት
አንጋጫ ከተማ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጎፋ ባረንቼ፣ ጂንካ ከተማ፣ አረካ ከተማ፣ ሾኔ ከተማ፣ ነጌሌ ቦረና፣ ሀዲያ ሌሞ፣ ጎባ ከተማ፣ ሮቤ ከተማ
የውድድር ቦታ: 1ኛ ዙር – ሶዶ | 2ኛ ዙር – ሀዋሳ
ወደ ማጠቃለያ ዙር የሚያልፉ ክለቦች – ሦስት
የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር
አንጋጫ ከተማ ከ ቡሌ ሆራ
ነጌሌ ቦረና ከ ሀዲያ ሌሞ
ሮቤ ከተማ ከ አረካ ከተማ
ጂንካ ከተማ ከ ሾኔ ከተማ
ጎፋ ባሬንቼ ከ ጎባ ከተማ
© ሶከር ኢትዮጵያ