​ከ20 ዓመት በታች የሊግ ውድድር የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የበላይነት የሚከወነው ከ20 ዓመት በታች የሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ ያሉ ውድድሮችን ዘንድሮ ለመከወን የተለያዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። ከ2008 ጀምሮ መደረግ የጀመረውን ከ20 ዓመት በታች ውድድርንም ለመከወን ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ከጥቅምት 9 – ታህሣሥ 30 ድረስ ምዝገባ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ አይዘነጋም። አሁን ደግሞ የዘንድሮ (2013) ውድድር ጥር 16 እንደሚጀምር ለክለቦች በተላከ ደብዳቤ ተገልጿል።

ከሳምንታት በፊት የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ በዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን የሚወዳደሩ ክለቦች ከ23፣ 17 እና 15 ዓመት በታች ቡድኖችን እንዲይዙ አቅጣጫ መቀመጡን እና በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚመራው ከ20 ዓመት በታች ውድድር እንዲቀር መወሰኑን በምትኩም ፌዴሬሽኑ ከ23፣ 20 እና 17 ዓመት በታች ውድድር መርጦ እንዲያወዳድር እንደሚደረግ ገልፀው ነበር። ይሁን እና አክሲዮን ማኅበሩ እስካሁን ከፌዴሬሽኑ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ባለመወያየቱ ከ2008 ጀምሮ ሲደረግ የነበረው ከ20 ዓመት በታች ውድድር ዘንድሮም እንደሚደረግ ተጠቁሟል። 

ዓምና የነበረው ከ20 ዓመት በታች ውድድር የመጀመሪያ ዙር መገባደጃ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት መቋረጡ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ