​ሊግ ኩባንያው እና ዲኤስቲቪ ይፋዊ ስምምነት ሊያደርጉ ነው

በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ተከትሎ ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የሊግ ኩባንያው እና ዲኤስቲቪ ይፋዊ ስምምነት በዚህ ሳምንት በሸራተን ሆቴል ሊያደረግ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2013 የፕሪምየር ሊግ ውድድር የቀጥታ ቴሌቭዥን ስርጭት ማስተላለፍ ለሚችሉ ድርጅቶች በአወጣው ጨራ መሠረት ሱፐር ስፖርት ውድድሩን በዲ ኤስቲቪ (Dstv ) በቀጥታ ለማስተላለፍ ማሸነፉ ይታወቃል፡፡ ስምምነቱ በግልፅ አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቢቆዩም ለዚህ ምላሽ ለመስጠት የፊታችን ዓርብ ኅዳር 25 ቀን 2013 ከምሽቱ 11፡30 አጠቃላይ ስምምነት እና ስርጭቱን በተመለከተ በሁለቱ ወገኖች መካከል የፊርማ ሥነ ስርዓት በሸራተን አዲስ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ