ከፍተኛ ሊግ | ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን የቀድሞ አሰልጣኙን ሾመ

አሰልጣኝ ኃይለየሱስ ጋሻው የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል፡፡

በአማራ ሊግ ተወዳዳሪ የሆነውንየሆነው ሸዋሮቢት ከተማን በማሰልጠን ጅማሮን ያደረጉት አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በሁለት አጋጣሚ ደብረብርሃን ከተማን እንዲሁም ደሴ ከተማን ማሰልጠን የቻሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ደብረብርሃን በማቅናት በአንድ ዓመት ውል ለማሰልጠን ተረክበዋል፡፡ 

ክለቡ በቀጣዩ ቀናት አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ዝግጅት እንደሚገባ አዲሱ አሰልጣኝ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ