የዐፄዎቹን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቀዋል

የፊታችን እሁድ የሚደረገውን የፋሲል ከነማ እና ዩ ኤስ ሞናስቲርን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቀዋል።

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የፊታችን እሁድ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ያከናውናል። ወደ ሞናስቲር በማቅናት 2-0 ተረተው የተመለሱት ዐፄዎቹም የመልሱን ጨዋታ ለማድረግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። 

ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ወሳኝ የሆነውን ይህንን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞችም መለየታቸው ታውቋል። በዚህም ከኮሚሽነሩ ውጪ ያሉት ሁሉም ዳኞች ከሩዋንዳ የመጡ ናቸው። ዋና ዳኛ ሳሙኤል ኡዊኩንዳ እንዲሁም ረዳቶች ቲዮኔ ንዳጂማና እና አብሮይስ ሀኪዚማና ሲሆኑ አራተኛ ዳኛ ደግሞ ሊዊዝ ሀኪዚማና መሆናቸው ተረጋግጧል። የጨዋታው ኮሚሽነር ደግሞ ደቡብ ሱዳናዊው ኦሞርሆ ሴስቲሊዮ ናቸው።

የዚህ መርሐ-ግብር የድምር ውጤት አሸናፊ በቀጣይ የአንደኛ ዙር የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታውን ከአህሊ ትሪፖሊ ጋር ያከናውናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ