አዳማ ከተማ ተከላካይ አስፈረመ

ትዕግስቱ አበራ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡

አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የነበረው ክለቡ በዛሬው ዕለት የመሐል እና የመስመር ተከላካይ የሆነው ትዕግስቱ አበራን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ ከዚህ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ፣ ሀላባ ከተማ፣ ሀምበሪቾ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የነበረው ተከላካዩ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ተሰረዘው የውድድር አመት ድረስ በሀዲያ ሆሳዕና ቆይታን ካደረገ በኋላ ለ2013 የውድድር ዓመት ማረፊያውን አዳማ አድርጓል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ