የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊገ በአዲስ ስያሜ እንደሚደረግ ታውቋል።
ዓምና ራሱን ችሎ በአክሲዮን ማኅበርነት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር ዓመት ውድድሩን በተለየ መልክ ለማድረግ እየተዘጋጀ ይገኛል። ማኅበሩም ሊጉን በቀጥታ በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ከዲ ኤስ ቲቪ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። ሊጉን በሱፐር ስፖርት እንዲተላለፍ ከማድረግ በተጨማሪ የሊጉ ስያሜ በቤት ኪንግ ተቋም እንዲሰየም ስምምነት ላይ መደረሱም ተገልጿል።
አክሲዮን ማኅበሩ ሊጉን ለማስላለፍ ጨረታ በሚያወጣበት ጊዜ ስያሜውንም ለመሸጥ መወሰኑ ሲገለፅ ነበር። ይህን ተከትሎ የሁለቱንም መብት ያሸነፈው ዲ ኤስ ቲቪ ሊጉን በቀጥታ ከማስተላለፉ በተጨማሪ ስያሜውን ከአጋር ድርጅቱ ቤት ኪንግ ጋር በመሆን ስያሜውን መውሰዱ ተገልጿል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ” በመባል እንደሚሰየም ተጠቁሟል።
© ሶከር ኢትዮጵያ