​ሀድያ ሆሳዕና የቀድሞ ተጫዋቹን  አስፈረመ

ዱላ ሙላቱ ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቀለ። 

ከዚህ ቀደም በሀዲያ ሆሳዕና መጫወት የቻለው. ፈጣኑ የመስመር ተጫዋች ቡድኑ በ2008 መጨረሻ ክለቡን ከለቀቀ በኃላ በደቡብ ፖሊስ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በአዳማ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዳማ ከተማ ለመቀጠል ቅድመ ስምምነት የፈፀመ ቢሆንም የቀድሞው አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቅሏል፡፡ ወደ ቀድሞ ክለቡ በመመለሴ ደስተኛ መሆኑን እና ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ እንደተዘጋጀም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ