​ሳላዲን ሰዒድ በቀጣይ ሳምንት ፈረሰኞቹን ይቀላቀላል

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ በቀጣይ ሳምንት ቡድኑን ይቀላቀላል።

በ2012 የውድድር ዘመን በኮሮና ምክንያት ውድድሩ እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ከጉዳት ጋር እየታገለ ፈረሰኞቹን እያገለገለ የቆየውና በቤተሰብ ሁኔታ ምክንያት ለወራት ከሀገር ውጭ የነበረው ሳላዲን በቅርቡ ወደ ሀገሩ መመለሱ ይታወቃል።

የቅድመ ዝግጅት ጊዜውን ቢሾፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ እያደረገ የሚገኘው ቡድኑ አንጋፋውን አጥቂ ሳላዲን ሰዒድን በቀጣዩ ሳምንት እንደሚያገኝ ለማረጋገጥ ችለናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ