በአዲሱ የሊጉ መርሐ-ግብር መሠረት የሸገር ደርቢ የሚደረግበት ሜዳ ለውጥ ተደርጎበታል

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል የሚደረገው የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የሚደረግበት አዲስ ቦታ ታውቋል።

በሀገራችን ከሚገኙ ትላልቅ የደርቢ ጨዋታዎች መካከል ቀዳሚ የሆነው የሸገር ደርቢ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ እንዲደረግ ቀድሞ መርሐ-ግብር ተይዞለት ነበር። ሊጉን በበላይነት የሚያስተዳድረው አክሲዮን ማኅበሩ ጨዋታዎች በልዩ ሁኔታ መደረጋቸውን ተከትሎ ይህ ተጠባቂ ጨዋታ ጅማ ስታዲየም ላይ እንዲደረግ በዕጣ መውጣቱን ገልፆ ነበር። ነገር ግን በትግራይ ክልል የሚገኙ ክለቦች (መቐለ 70 እንድርታ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ እና ስሑል ሽረ) በውድድሩ የመሳተፋቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ አክሲዮን ማኅበሩ ተለዋጭ መርሐ-ግብር አውጥቶ ለክለቦች በትኗል።

በወጣው አዲስ መርሐ-ግብር መሠረትም ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ እሁድ ታህሣሥ 27 ከረፋዱ 4 ሰዓት በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ተረጋግጧል።

© ሶከር ኢትዮጵያ