​ወልቂጤ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

የመሐል ተከላካዩቹ አሌክስ ተሰማ እና አሚኑ ነስሩ ወልቂጤ ከተማን ለመቀላቀል ተስማሙ፡፡ 

በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ የመሳተፋቸው ጉዳይ ያከተመ የሚመስለው የትግራይ ክልል ክለቦች ተጫዋቾች ወደተለያዩ ክለቦች እያመሩ ይገኛሉ። በእነኚህ ክለቦች ውስጥ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የሆኑት አሌክስ ተሰማ እና አሚኑ ነስሩ ከሰሞኑ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ልምምድ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን በጥቂት ቀናትም ውስጥ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ 

ከዳሽን ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን አምስት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረውና ዘንድሮ ለስሑል ሽረ ለመጫወት ፊርማውን አኑሮ የነበረው ተከላካዩ አሌክስ እና ከጅማ አባጅፋር ወደ መቐለ ተጉዞ ከክለቡ ጋር ያለፉትን ሁለት ዓመታት ጥሩ ቆይታ ያደረገው ሌላኛው ተከላካይ አሚኑ ነስሩ በቀጣይ ቀናት የወልቂጤ ከተማ ተጫዋቾች መሆናቸው ዕርግጥ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ