ከፍተኛ ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ በርካታ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል አድሷል

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር የተደለደለው አቃቂ ቃሊቲ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ስምንት ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ ተጫዋቾችን ኮንትራት ደግሞ አድሷል፡፡

በቅርቡ አሰልጣኝ ዳዊት ታደለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ተወዳዳሪው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሳምንት በፊት ወደ ልምምድ የገባ ሲሆን አሰልጣኙ አዲስ ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች መካከል ከዚህ ቀደም ከነበሩበት ገላን ከተማ የመጡ ቁጥራቸው ላቅ ያለ ነው፡፡

አዳዲስ ፈራሚዎች

ግብ ጠባቂ – ተመስገን ጮኖሬ (ከገላን)

ተከላካዮች – አንተነህ መለሰ (ከገላን) ፣ አዲሱ ሰይፉ (ከመድን)፣ ዮናታን አምባዬ (ከገላን)፣ ሄኖክ ካሳሁን (ከገላን)፣ ዮናስ አቡሌ (ከመቂ)

አማካዮች – ዳዊት ተፈራ (ከገላን)፣ ምንተስኖት መንግሥቱ (ከገላን)፣ ፊሊሞን ወልደፃዲቅ (ከገላን)

አጥቂዎች – ሱራፌል አየለ (ከባቱ)፣ ናድር አክመል (ከንስር)፣ ሄኖክ (ከወልዋሎ) እና እሸቱ ጌታሁን (ከገላን)

ውል ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች

አዝማች ወልደገብርኤል፣ ከድር አድማሱ፣ ጌትነት ታፈሰ፣ ሳምሶን ተሾመ፣ ጥላሁን ወልዴ፣ ዘመን አበራ፣ ሱልጣን ከድር እና እስማኤል አደም


© ሶከር ኢትዮጵያ