ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ የተደለደለው ደሴ ከተማ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን በዋና አሰልጣኝነት ከሳምንት በፊት የቀጠረው ደሴ ከተማ የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ ሌሎች አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ደግሞ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡ ውል ያደሱት ተጫዋቾች አብደላ እሸቱ ፣ አብዱልአዚዝ ዳውድ ፣ አንዋር መሀመድ ፣ አንሷር መሀመድ እና ዓዲስአለም ዘውዱ ሲሆኑ ግብ ጠባቂው እድሪስ አብዱ ፣ ተከላካዩ ሠለሞን ሀብቱ ከወሎ ኮምቦልቻ ፣ አማካዩ ሙሉቀን አሰፋ ከጎጃም ደብረማርቆስ ፣ ሌላኛው አማካይ አዳነ ተካ ከአክሱም ደግሞ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾቹ ሆነዋል፡፡

ከቀናት በፊት ልምድድ የጀመረው ክለቡ እስከ አሁን የዘጠኝ ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ ስምንት አዳዲሶችን ደግሞ ወደ ቡድኑ አካቷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ