ከፍተኛ ሊግ | ለገጣፎ ለገዳዲ ተጨማሪ አምስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

የምድብ ሀ ተሳታፊው ለገጣፎ ለገዳዲ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

የአሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙን ኮንትራት ካራዘሙ በኃላ በርከት አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን አስፈርመው የነበሩት ለገጣፎ ለገዳዲዎች በምድብ ሀ ስር በባቱ ከተማ በሚደረገው ውድድር ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ክለቡ ያለፉትን ሳምንታት በባቱ (ዝዋይ) ነባር እና አዳዲስ ተጫዋቾች በመያዝ ዝግጅቹን ሲሰራ የሰነበተ ሲሆን ተጨማሪ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አክሏል፡፡ የቀድሞው የመድን፣ ንግድ ባንክ፣ አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ አማካይ ሲሳይ ቶሌ፣ ታምራት ዘውዴ (ከለገጣፎ አካባቢ አማካይ) ፣ ፋሲል ባቱ (ከሀምበሪቾ አማካይ)፣ ሲሳይ አቡሌ (ከዱከም አጥቂ)፣ ሀብታሙ ወርቁ )ከወሎ ኮምቦልቻ አጥቂ) ክለቡን መቀላቀል የቻሉ አዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡

ክለቡ እስከ አሁን በድምሩ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ነባር ውል ያራዘሙት ቁጥር ደግሞ አስራ ስድስት ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ