ከፍተኛ ሊግ | ነገሌ አርሲ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈረመ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ላይ የሚገኘው ነገሌ አርሲ የአሰልጣኙን ውል ያራዘመ ሲሆን አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ደግሞ አስፈርሟል፡፡

በምድብ ሐ የከፍተኛ ሊጉ ተወዳዳሪ አርሲ ነገሌ ከተማ አምና ክለቡን የተረከቡትን አሰልጣኝ ታዬ ናኒቻን ለተጨማሪ አመት ለማቆየት በመስማማት ከአሰልጣኙ ጋር መቀጠሉ የተረጋገጠ ሲሆን አሰልጣኙም ከሰሞኑ ለበርካታ ተጫዋቾች የሙከራ ዕድል እንዲሁም ደግሞ በቀጥታ ከክለብ የተመለከቷቸውን አስራ አራት ተጫዋቾች በማስፈረም ወደ ልምምድ ገብተዋል፡፡

ግብ ጠባቂዎች – ኤፍሬም ኃይሉ (ከፌዴራል ፖሊስ)፣ ሚኪያስ ዶጂ (ከአቃቂ)

ተከላካዮች – ዘውዱ መና (ከፌድራል ፖሊስ)፣ ማሩፍ መሐመድ (ከፌዴራል ፖሊስ)፣ ቱፋ ተሺታ (ከካፋ ቡና)፣ ዘላለም (ከደቡብ ፓሊስ)፣ መታሰቢያ ገዛኸኝ (ከሺንሺቾ)፣ ጫላ ተስፋዬ (ከነገሌ ቦረና)፣ አያልቅበት ነገዎ (ከዱከም)

አማካዮች – በረከት ግዛው (ከወልዲያ)፣ በላይ ያደሳ (አክሱም)፣ ሙህዲን አብደላ (ከሻሸመኔ)፣ መሳይ ወንድሙ (ከሻሸመኔ)

አጥቂዎች – ፀጋው ታዬ (ከመተሀራ) ምትኩ ጌታቸው (ከጌዲኦ ዲላ)


© ሶከር ኢትዮጵያ