የ2013 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀመርበት ቀን በሁለት ሳምንት መራዘሙ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ውድድር በሁለተኛ እርከን ላይ የሚገኘው ከፍተኛ ሊግ በጁፒተር ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ታኅሣሥ 10 በሦስት የተለያዩ ቦታዎች በመቀመጥ ውድድሮች እንደሚጀምሩ መገለፁ ይታወሳል።
ሆኖም ውድድሩ ወደ ታኅሣሥ 24 መለወጡን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘው መረጃ የሚጠቁም ሲሆን ቡድኖች የመመዝገቢያ ክፍያ አለመክፈላቸው እንደምክንያትነት ተጠቅሷል።
ከሊጉ ጋር በተያያዘ መረጃ በያዝነው ውድድር ዓመት ከሚሳተፉ 36 ክለቦች መካከል ሁለት ቡድኖች በክፍያ ምክንያት እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳይ ደግሞ ሦስት የትግራይ ቡድኖች ላይሳተፉ ይችላሉ ተብሏል።
© ሶከር ኢትዮጵያ