ለሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች እፎይታን የፈጠረ ተግባር ተፈፀመላቸው

በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ ተሳታፊ የሆኑ አስር ክለቦች ለኮቪድ 19 ምርመራ በየጨዋታው ወጪ የሚያወጡትን ብር ሙሉ በሙሉ ያስቀረ መልካም ተግባር በአንድ ክልል ተፈፀመላቸው፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር መቐለ 70 እንደርታን ብቻ ሳያካትት በሀዋሳ ከተማ የሰው ሰራሽ ሳር ከጀመረ እነሆ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል፡፡ ዘንድሮ ክለቦች ካለፈው ዓመት በይበልጥ ለተጨማሪ ወጪ በኮቪድ 19 ሳቢያ የተዳረጉ ሲሆን በራሳቸው ገንዘብ ክለቦች ከጨዋታ ቀደም ብሎ በየጊዜው ከ72 ሰዓት በፊት ለተጫዋቾቻቸውን እና ለቡድኑ አጠቃላይ አባላት ተፈጻሚ እንደሚሆን ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ ባስቀመጠው አቅጣጫ ላይ የተገለፀ ቢሆንም ክለቦች በየጊዜው ለዚህ ህክምና የሚያወጡትን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሲዳማ ክልል መንግስት ሸፍኖላቸዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ሀዋሳ ላይ እየተደረገ ባለው የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ላይ በአጠቃላይ 45 ጨዋታዎችን የሚደርጉ ሲሆን በአንድ ሳምንት ከአራት መቶ ሺህ ብር በላይ ሊያወጡት የነበረውን የህክምና ወጪ ነው ክልሉ መሸፈን የቻለው። በአጠቃላይ በመጀመሪያው ዙር ከአስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ለኮቪድ 19 ምርመራ ሊያወጡት የነበረውን ገንዘብ በራሱ ወጪ የሸፈነው። ለዚህም መልካም ተግባር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የምስጋና ፕሮግራም እንደሚያቀርብ የሰማን ሲሆን ክለቦችም ክልሉ ላደረገላቸው ድጋፍ እያመሰገኑ ይገኛሉ፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ