አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በቦታቸው ሆነው ለምን ቡድናቸውን አልመሩም ?

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ጨዋታቸውን በመልካም ሁኔታ የጀመሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ያለ ዋና አሰልጣኛቸው ውድድራቸውን ለምን ጀመሩ ?

ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በይፋ አስፈርሞ ራሱን ለዚህ ዓመት ውድድር ሲያዘጋጅ ቆይቶ ትናንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ጨዋታውን ወላይታ ድቻን በማሸነፍ በድል ጀምሯል። በትናንትናው ጨዋታ ወቅት ዋና አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለ ቡድናቸውን በቴክኒክ ቦታ ላይ በመቀመጥ ያልመሩ መሆናቸውን ስንመለከት በአንፃሩ በኩቡር ቲሪቩን በመቀመጥ የተለያዩ መልክቶችን ሲለዋወጡ እንደነበረ ታዝበናል።

አሰልጣኙ ቡድናቸውን ያልመሩበት ምክንያት ምድነው ብለን ስንጠይቅ ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ጋር ሀዲያ ጋር ያልጨረሰው ጉዳይ እንዳለ ሰምተናል። አሰልጣኝ ፀጋዬ ከሆሳዕና ጋር እስከ እዚህ ዓመት ጥር ወር ድረስ ኮንትራት ያላቸው በመሆኑ ሀዲያ ሆሳዕናዎች አሰልጣኝ አሸናፊን በግልፅ መጠቀም ስለማይችሉ እና ክስ እንዳይመሰረትባቸው በመስጋት በቴክኒክ ቦታ ላይ እንዳይቀመጡ አድርገዋል። ይህን ተከትሎ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እስከ ጥር ወር መጀመርያ ድረስ ቡድናቸውን በቦታቸው ተቀምጠው የማይመሩ ይሆናል ማለት ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ