ብርሀኑ ግዛው በሉሲዎቹ አሰልጣኝነት ይቀጥላሉ

አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውላቸው እንደሚራዘም ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሐምሌ ወር 2012 መጨረሻ ላይ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ የተነሳ ምንም አይነት ውድድሮች አይካሄዱም ማለቱን ተከትሎ በተለያየ የዕደሜ ዕርከን ውስጥ ተሹመው የነበሩ እንዲሁም የዋናው የወንድ እና ሴት ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ውላቸው እንደማይራዘም ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ሆኖም አሁን ላይ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኞችን በአዲስ መልክም ሆነ ውል በማራዘም ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ ብርሀኑ ግዛው በሉሲዎቹ አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ወስኗል። አሰልጣኙ ሀዋሳ ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እያሰለጠነ በፕሪምየር ሊጉ ውድድር ላይ የሚገኝ ሲሆን በያዝነው ሳምንትም አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ አምርተው ውሉ የሚያራዝሙበትን ፊርማ ያኖራሉ ተብሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ