ወልቂጤ ከተማ ከጅማ አባጅፋር አቻ የተለያዩበት ጨዋታ መጠናቀቅ ተከትሎ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል።
ጳውሎስ ጌታቸው – ጅማ አባጅፋር
ስለ ጨዋታው
” በውጤቱ ብዙ አልተከፋሁም። ምንም ዓይነት የወዳጅነት ጨዋታ ስላላደረግን የዛሬው ጨዋታ ገና ሁለተኛ ጨዋታችን ነው። ከእረፍት በፊት ያጀኘናቸውን ሦስት አጋጣሚዎች አስቆጥረን ቢሆን ኖሮ የጨዋታው ውጤት ይቀየር ነበር። የወዳጅነት ጨዋታዎች አለማድረጋችን ወደ ጎል በምናደርጋቸው ሙከራዎች ላይ ይበልጥ ጎድቶናል። ሌሎች ቡድኖች ወደ ውድድር ገብተዋል እኛ ግን ገና ወደ ወዳጅነት ጨዋታ እየገባን ነው።”
ደግአረግ ይግዛው – ወልቂጤ ከተማ
ስለ ጨዋታው
“በውጤቱ ደስተኛ አይደለሁም፤ ነገርግን በእግርኳስ የሚከሰት ነው። ልጆቼ በጨዋታው የተቻላቸውን አድርገዋል። ነገርግን ጨዋታው ባሰብነው መልኩ አልሄደልንም።”
ቡድኑ ስለሚስተዋልበት ዕድሎችን የመጨረስ ችግር
” ልጆቻችን በአብዛኛዎቹ ወጣቶች ከመሆናቸው አንፃር የልምድ እጥረት አለ። በተጨማሪም ውጤት ይዞ ለመውጣት ከፍተኛ ጉጉት አለ ከዚህ መነሻነት ክፍተቶች ይስዋሉብናል ይህን በቀጣይ ለመቅረፍ እንሰራለን።”
ከጨዋታ ውጭ ስለተባሉባቸው ኳሶች እና ዳኝነቱ
“በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ማለት አልፈልግም። ይህን የሚከታተል የዳኞች ኮሚቴ አለ። ስለዚህ የዛሬውን የባለፈውንም ጨዋታውን ተመልክቷል ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ መመዘን ያለበት ኮሚቴው ነው።”
© ሶከር ኢትዮጵያ