የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 1-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 3-1 ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል።


ፍስሐ ጥዑመልሳን – ድሬዳዋ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው በመሀል ሜዳ ላይ ያመዘነ ተመጣጣኝ ጨዋታ ነበር ፤ በሰራናቸው ጥፋቶች ከተሰጡብን ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች በኃላ የእኛ ልጆች የመውረድ እና የመከፋፈት ነገሮች ተስውሎባቸዋል። ይህን ክፍተት ለማስተካከል የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ ብናደርግም ተሸንፈናል።”

ስለ ሁለቱ ፍፁም ቅጣት ምቶች የተሰጡበት መንገድ

” ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በተሰጠን ሰነድ ሆነ በነበሩ ውይይቶች ከአንድ ክለብ ከ10 በላይ ደጋፊ አይገባም ተብለን ነበር ፤ ዛሬ የሆነው ግን ሌላ ነው እኛ 11ኛ ሰው እንኳን ሳይፈቀድልን በተጋጣሚያችን በኩል ከ50 እስከ 60 የሚሆኑ ደጋፊዎች ገብተው ነበር። ሁለተኛ አቀማመጡም ልክ አልነበረም። በኮቪድ 19 ምክንያት ሰው ከሜዳ ቢከለከልም በዚህ ደረጃ ሰዎች ተሰብስበው እንዲጨፍሩ መደረጋቸው አድሎ ነው። ሌላው እኛ ቅጣት ምት ሆነ ፍፁም ቅጣት ምት ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን አግኝተን ነበር ነገርግን ለእኛ አልተነፋልንም። መሰል የዳኞት ከተፅዕኖ ያለመውጣት ነገሮች እስከቀጠሉ እንዴት ነው እግርኳሳሳችንን ማሳደግ የሚቻለው።”

ቡድኑ በማጥቃቱ ረገድ ማሻሻል ስለሚገባው ጉዳይ

“በስብባችን እስካሁን ልምምድ ያልሰሩ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚገኘው ኢታሙና ኬይሙኒ ሲጨመሩ ይሻሻላል። አስቻለው በዛሬው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ከቡድኑ ጋር ሁለት ልምምድ ስለሰራ ነው።ስለዚህ ስህተቶች በማረም ለቀጣይ ጨዋታዎች በጥንካሬ እንቀርባለን።”

ማሒር ዴቪድስ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው

“በርካታ ቀሪ ስራዎች ቢኖሩንም የተሻለ ጨዋታ ነበር።በዛሬው ጨዋታ የፈጠርናቸው እድሎች በተለይ በመጀመሪያ አጋማሽ የፈጠርናቸውን እድሎች ወደ ጎልነት መቀየር ረገድ መስራት ይገባል ፤ ዋናው ነገር ማሸነፋችን እና ሦስት ነጥብ ማግኘታችን ነው።”

በመጨረሻ ደቂቃ ስለተቆጠረባቸው ግብ

“ባሳለፍነው ሳምንት እንደተናገርኩት የትኩረት ማጣት በተወሰኑ ተጫዋቾች ላይ ዛሬም ይስተዋል ነበር በዚህም ቅር ተስኝቻለው። ነገርግን ዋናው ሶስት ግቦችን እና ሶስት ነጥብ ማግኘታችን ቢሆኖም አሁንም የሚቀሩን ብዙ ስራዎች አሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ