በሚዲያ አካላት ላይ የተፈጠረውን ቅሬታ ሊግ ኩባንያው እንደሚያስተካከል አስታወቀ

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ጅማሮውን ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚዲያ አካላት ላይ የተፈጠረውን መንገላለታት አስመልክቶ በትናንት ጠዋት ዘገባችን ላቀረብነው ምልከታ ምላሽ ተሰጠ።

የዘንድሮው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከቀደምት ዓመታት በተለየ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት በማግኘቱ ለስፖርት ቤተሰቡም ሆነ ለመገናኛ ብዙሃን አካላት የተሻለን አማራጭ እየፈጠረ ይገኛል። ከስርጭቱ ባሻገር ቁጥራቸው ጥቂት የሚባሉ የመገናኛ ብዙሃን አባላትን ጨዋታዎችን ለመታደም ወደ ስታዲየም ማምራታቸው አልቀረም። ሆኖም እነዚሁ አባላት ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ለመግባት ብሎም ከተገባ ወዲህ መቀመጫ ለማግኘት የሚያልፉት ውጣ ውረድ ግን እጅግ አድካሚ ብሎም “ስለምን ወደ ስታዲየም መጣሁ?” የሚያስብሉ መሆናቸውን ባለፉት ሁለት የጨዋታ ሳምንታት መታዘብ መቻላችንን የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች ላይ መፃፋችን ይታወቃል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሊግ ኩባንያው ባደረገው ስብሰባ ችግሩ መኖሩን አምኖ የተፈጠረው ችግርም ከኮቪድ ፕሮቶኮል ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ አለመረዳቶች የተከሰተ እንደሆነና በቀጣይ በሚኖሩ ጨዋታዎች መገናኛ ብዙኃን በቀኝ ጥላ ፎቅ ቋሚ በር እንደተዘጋጀና ይህን የሚያስፈፅሙ ባለሙያ መመደቡን ሰምተናል። በዚህም መሠረት ለውድድሩ መድመቅ የስፖርት ሚዲያው ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንዳለው ሊግ ካምፓኒው እንደሚረዳ በመግለፅ የሚዲያ አካላት ያለምንም ችግር መጥተው እንዲዘግቡ አሳውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ