የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን በሀዋሳ እንደቀጠለ ነው፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ ጥሩ እንቅስቃሴን ከሚያደርጉ ተጫዋቾች ጋር ቆይታን የምታደርግ ሲሆን ዛሬም ከባለክህሎቷ አማካይ ጋር አጭር ቆይታ አድጋለች።
ትናንት በሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ አቃቂ ቃሊቲ ከ ጌዲኦ ዲላ 1ለ1 ቢለያይም አቃቂ ቃሊቲን ዘንድሮ የተቀላቀለችው አማካይዋ ዙለይካ ጁሀድ አስደናቂ ብቃት ማሳየት ችላለች፡፡ በመከላከያ የእግር ኳስ ህይወቷን የጀመረችው እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሳኩ ስድስት ዓመታትን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥም ጥሩ ጊዜ ያሳለፈችው ተጫዋቿ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ክለቧ ሶስት ነጥብ ማግኘት ባይችልም ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገች የምትገኝ ሲሆን ስለ ዘንድሮ እቅዷ ተከታዩን አጭር ሀሳብ ሰጥታናለች፡፡
“ከፈጣሪ ጋር ደረጃ ውስጥ ለመግባት ነው ጥረታችን። ነገር ግን ብዙ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው እንቅፋት እየሆነብን ነው። ቢሆንም ለመውረድ ሳይሆን ከአንድ እስከ ሦስት ለማጠናቀቅ እንሠራለን፡፡ በግሌም እንደ ቡድንም ጥሩ ውጤትን አምጥተን ደስተኛ ሆኜ መጨረስን እፈልጋለሁ፡፡ ከፈጣሪ ጋር ኮከብ ተጫዋች ሆኜ ዓመቱን መጨረስም ፍላጎቴ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቁ ደረጃ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ነው እኔም ጠንክሬ ሰርቼ መመለስ እፈልጋለሁ። አሁን ከጉዳት አገግሜ መጥቻለሁ። በቀጣይም ጤና ይስጠኝ እንጂ ሀገሬን በደንብ ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ።”
© ሶከር ኢትዮጵያ