የፊፋ 2021 ኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ዳኞች ታውቀዋል

የዓለም አቀፋ እግርኳስ ማኅበር (ፊፋ) በ2021 የፊፋ ኢንተርናሽናል ዳኞች በመሆን የሚያገለግሉ ኢትዮጵያዊ ዋና እና ረዳት ዳኞችን ስም ዝርዝር ማሳወቁን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2021 በኢንተርናሽናል ዳኝነት የሚያገለግሉ 7 የወንድ እና 4 የሴት ዋና ዳኞች እንዲሁም 6 የወንድ እና 4 የሴት ረዳት ዳኞች መስፈርቱን በሟማላት ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን ከረዳት ዳኞች አንዱ በኢንተርናሽናል ዳኝነት ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በዋና ዳኝነት ከተመረጡት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቪዲዮ ዳኝነትም ተመርጧል፡፡ በአጠቃላይ በቀጣዩ የውድድር ዘመን 21 ኢንተርናሽናል ዋና እና ረዳት ዳኞች ኢትዮጵያን በመወከል ውድድር የሚመሩ ይሆናል፡፡

የዳኞች ዝርዝር

ዋና ወንድ ዳኞች

1 በዓምላክ ተሰማ
2 በላይ ታደሰ
3 ብሩክ የማነብርሃን
4 ቴዎድሮስ ምትኩ
5 ለሚ ንጉሴ
6 አማኑኤል ኃይለሥላሴ
7 ኃይለየሱስ ባዘዘው

ሴት ዋና ዳኞች

1 ሊዲያ ታፈሰ
2 ፀሐይነሽ አበበ
3 አስናቀች ገብሬ
4 መዳብ ወንድሙ

ረዳት ወንድ ዳኞች

1 ክንዴ ሙሴ
2 ትግል ግዛው
3 ሸዋንግዛው ተባበል
4 ተመስገን ሳሙኤል
5 ፋሲካ የኋላሸት
6 ይበቃል ደሳለኝ

ረዳት ሴት ዳኞች

1 ወይንሸት አበራ
2 ይልፋሸዋ ካሣሁን
3 ብርቱካን ማሞ
4 ወጋየሁ ዘውዱ


© ሶከር ኢትዮጵያ