የከፍተኛ ሊግ የጠዋት መርሐ ግብር ሳይካሄድ ቀርቷል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ሊካሄድ የነበረው የካፋ ቡና እና ሻሸመኔ ከተማ ጨዋታ ሴይዋሄድ ቀርቷል።

2:00 ሊጀመር መርሐ ግብር ወጥቶለት ለነበረው ጨዋታ የካፋ ቡና ተጫዋቾች በሜዳ ላይ የኮቪድ 19 ህግን አክብረው ቢገኙም ሻሸመኔ ከተማዎች በአንፃሩ ምንም አይነት የምርመራ ውጤትን ባለማቅረባቸው በህጉ መሠረት የተገኘውን ካፋ ቡናን ዳኞቹ ሰላሳ ደቂቃ ሳይጠብቁ ሸኝተዋቸዋል፡፡የዚህም ውጤት በቀጣዮቹ ቀናት የሚገለፅ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ በሜዳ ላይ ተገኝታ ባደረገችው ማጣራት በጤና ህጉ የፕሮቶኮል መመሪያ መሠረት ካፋ ቡናዎች ሦስት ነጥቡን እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ዛሬ በሦስት ጨዋታዎች ሲቀጥል ሀዋሳ ላይ 04:00 አቃቂ ቃሊቲ ከ ጅማ አባ ቡና፣ 10:00 ላይ ቤንች ማጂ ከ ጋሞ ጨንቻ እንዲሁም ድሬዳዋ ላይ 09:00 ጌዴኦ ዲላ ከ ኮልፌ ቀራኒዮ ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ