የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ሴቶች ከፍተኛ ዲቪዝዮን የ2008 የውድድር ዘመን ሀሙስ በ8 ክለቦች መካከል ተጀምሯል፡፡
የሴቶች እግርኳስ በኢትዮጵያ የእግርኳስ ካርታ ላይ እንዲሰፍር ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይህንን ውድድር ከ1995 ጀምሮ ሲያዘጋጅ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
የ1ኛ ሳምንት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
ቦሌ 1-1 ጉለሌ
አስኮ 1-0 አቃቂ
ቂርቆስ 4-0 አሜን
ብሩህ ተስፋ ለኢትዮጵያ 9-1 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ
የ2ኛ ሳምንት ቀጣይ ጨዋታዎች በመጪው ሐሙስ የሚደረጉ ሲሆን ውድድሩን እየተከታተልን ወደእናንተ የምናደረስ ይሆናል፡፡
ያጋሩ