በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ቪክቶሪያ ላይ የሲሸልሱን ሻምፒዮን ሴንት ሚሸል ዩናይትድን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይቷል፡፡ ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው ጨዋታ 3-0 አዲስ አበባ ላይ በማሸነፋቸው በድምር ውጤት 4-1 በመርታት ወደ አንደኛው ዙር አልፈዋል፡፡
ግብ በማግባት ቅድሚያውን የያዙት ጊዮርጊሶች ሲሆኑ በመጀመሪያው አጋማሽ የመስመር አጥቂው ራምኬል ሎክ ኳስን ከመረብ አዋህዷል፡፡ ጊዮርጊስ በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠረበት ግብ 1-1 ሊለያይ ችሏል፡፡
ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው የማጣሪያ ዙር በሜዳቸው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ክለብ ቲፒ ማዜምቤን ከመጋቢት 4-6 ባሉት ቀናት ውስጥ ያስተናግዳሉ፡፡ ቲፒ ማዜምቤ የወቅቱ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ሲሆን በሳለፍነው ሳምንት የቱኒዚያውን ኤቷል ደ ሳህልን 2-1 በማሸነፍ የካፍ ሱፐር ካፕን ለሶስተኛ ግዜ አንስቷል፡፡
ያጋሩ