ጅማ አባ ጅፋር ከ ሀዋሳ ከተማ – አሰላለፍ

የአምስተኛ ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

የአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጅማ አባ ጅፋር በድሬዳዋው ጨዋታ ከተጠቀመበት ቡድን ጄይላን ከማል እና ተመስገን ደረሰን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ በማምጣት አዳላሚን ናስር እና ሙሉቀን ታሪኩን ተክቷል። በውድድር ዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜም ሁለት ግብ ጠባቂዎችን በተጠባባቂ ወንበር ላይ ይዟል።

ኢትዮጵያ ቡናን በአስደናቂ ሁኔታ ካሸነፈው ቡድናቸው የአንድ ተጫዋች ለውጥ ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች ደግሞ የመስመር አጥቁው ኤፍሬም አሻሞን በብርሀኑ በቀለ ቤታ ተጠቅመዋል።

አሰላለፉ ይህንን ይመስላል:-

ጅማ አባ ጅፋር

1 ጄኮ ፔንዜ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
14 ኤልያስ አታሮ (አ)
26 ጄይላን ከማል
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
8 ሱራፌል አወል
22 ሳምሶን ቆልቻ
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ
17 ብዙዓየሁ እንዳሻው

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
2 ዘነበ ከድር
16 ወንድምአገኝ ማዕረግ
4 ምኞት ደበበ
12 ደስታ ዮሐንስ (አ)
5 ጋብሬል አህመድ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
19 ዮሐንስ ሰገቦ
17 ብሩክ በየነ

ቀጥታ የውጤት መግለጫ | LIVE SCORE


© ሶከር ኢትዮጵያ