ምስር አል ማቃሳ 3-0 መከላከያ
59’አምር ባራካት
72′ ኤልሰኢድ ሃምዲ
88′ ኦማር ኤል ናግዲ (ፍፁም ቅጣት ምት)
(ድምር ውጤት 6-1)
– – – – – – –
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በምስር አል ማቃሳ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ምስር በአጠቃላይ 6-1 ውጤት ወደ አንደኛው ዙር አልፏል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ ተጨማሪ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
88′ የተጫዋች ለውጥ መከላከያ
የፍፁም ቅጣት ምት ያሰጠው ሳሙኤል ሳሊሶ ወጥቶ መሃመድ ናስር ገብቷል፡፡
88′ ጎልልል
ኦማር ኤል ናግዲ የፍፁም ቅጣት ምቱን እጅግ በቀላሉ ይድነቃቸው በወደቀበት ተቃራኒ አስቆጥሯል፡፡
87′ የፍፁም ቅጣት ምት
ሳሙኤል ሳሊሶ ሁሴን ኤልሻሃት ላይ በሰራው ጥፋት ለማቃሳ የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡
79′ የተጫዋች ለውጥ – ምስር አል ማቃሳ
መሃመድ አትዋ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሆስኒ ፋቲህን ቀይሮ ገብቷል፡፡
72′ ጎልልል
ኤልሰኢድ ሃምዲ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሯታል፡፡
71′ ኦማር ሰኢድ ሁሴን ራጋብን ቀይሮ ገብቷል፡፡
* ማቃሳዎች በ2ኛው አጋማሽም በኳስ ቁጥጥር የበላይነታቸው ዘልቀዋል፡፡ በአዲስ አበባው ጨዋታ ድንቅ የነበረው ሃኒ ሰኢድ በዚህም ጨዋታ የማቃሳ እንቅስቃሴ መሪ ሆኗል፡፡
68′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
በሃይሉ ግርማ ወጥቶ ሳሙኤል ታዬ ገብቷል፡፡
65′ ከመሴመር የተሻገረውን ኳስ ይድነቃቸው ኪዳኔ ከኤልሰኢድ ሃምዲ ጋር ሲሻማ ተመትቶ ወድቋል፡፡
62′ የተጫዋች ለውጥ – ምስር አል ማቃሳ
አህመድ ሳሚ ወጥቶ ሁሴን ኤልሻሃት ገብቷል
59′ ጎልልል
አምር ባራካት ማቃሳን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
57′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ባዬ ገዛኸኝ ገብቶ ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቷል
46′ ሁለተኛው አጋማሸ ተጀመረ
– – – – – –
ተጠናቀቀ!!
የመጀመርያው አጋማሽ 0-0 ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
37′ ኤልሰኢድ ሀምዲ ከግራ መስመር አክርሮ የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡
30′ ምስር አል ማቃሳ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ይዟል፡፡ የመከላከያ እንቅስቃሴ በራሳቸው የግብ ክልል የተገደበ ሆኗል፡፡
21′ ሙሉቀን በአህመድ ሳሚ ላይ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ቅጣት ምት ማቃሳዎች ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
16′ ሙሉአለም ጥላሁን የማቃሳ ተከላካዮችን ስህተት ለመጠቀም እየጣረ ይገኛል፡፡
7′ ኦማር ናጅዲ በግምት ከ20 ሜትር ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
4′ ምስር አል ማቃሳዎች በግራ መስመር በኩል የግብ እድል ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡
1’መከላከያ በሳሙኤል ሳሊሶ አማካኝነት እጅግ ለግብ የቀረበ ሙከራ አድርጎ ግብ ጠባቂው አውጥቶበታል፡፡
1′ ጨዋታው በምስር አል ማቃሳ ጀማሪነት ተጀምሯል፡፡
02:54 በአሁኑ ሰአት ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡
02:45 ሁለቱም ቡድኖች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
– – – – – – –
የመከላከያ አሰላለፍ
ይድነቃቸው ኪዳኔ
ነጂብ ሳኒ – አዲሱ ተስፋዬ – ሙሉቀን ደሳለኝ – ቴዎድሮስ ወርቁ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን ቴዎድሮስ ታፈሰ – ሳሙኤል ሳሊሶ
ሙሉአለም ጥላሁን
– – – – – –
የምስር አል ማቃሳ አሰላለፍ
አህመድ መሶውድ
መሃመድ ጋቢ ሚዶ – አብድልሃሚድ ሳሚ – አህመድ ሰኢድ ኦካ – ሆስኒ ፋቲህ
ሃኒ ሰኢድ
አህመድ ሳሚ – ኦማር ኔግዲ – ኤልሰኢድ ሃምዲ
አምር ባራካት – ሁሴን ራጋብ