ባህር ዳር ከተማ ከ ፋሲል ከነማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች እነሆ።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በወልቂጤ ከተማ ከተረታው ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ጉዳት የገጠመው ዜናው ፈረደ፣ በረከት ጥጋቡ እና ግርማ ዲሳሳን በወሰኑ ዓሊ፣ ሄኖክ አወቀ እና ከጉዳት መልስ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሚያከናውነው አፈወርቅ ኃይሉ ተክተዋል።

ጉዳት ላይ የሰነበቱት ሰዒድ ሀሰን እና ሀብታሙ ተከስተን በተጠባባቂነት የያዘው ፋሲል ከነማ ግን ወላይታ ድቻን ሲያሸንፍ የተጠቀመበትን የመጀመሪያ አሰላለፍ ሳይለውጥ ለጨዋታው ቀርቧል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪስተን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
17 ሄኖክ አወቀ
14 ፍጹም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
8 ይሁን እንደሻው
10 ሱራፌል ዳኛቸው
7 በረከት ደስታ
12 ሳሙኤል ዮሐንስ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ