አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ላይ ተቃውሞ ቀረበባቸው

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ተጠባቂው የፋሲል ከነማ እና የባህር ዳር ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ላይ ተቃውሞ ቀርቦባቸዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የባህር ዳር ከተማ የዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ ከብዙ አስገራሚ ክስተቶች ጋር በሁለት አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል። ታዲያ ከጨዋታው መተጠናቀቀ በኃላ በቀኝ ከማን አንሼ በሚገኘው አቅጣጫ የነበሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በውጤቱ ደስተኛ ባለመሆን አሰልጣኝ ስዮም ከበደን ክለቡን እንዲለቁ በእጃቸው የያዙትን ፁሑፍ በማሳየት ተቃውሞ ሲያቀርቡ ተመልክተናል።

በሊጉ ጠንካራ ከሚባሉ ቡድኖች አንዱ የሆነው ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በቡድኑ እንቅስቃሴ እና ውጤታማነት ደስተኛ እንዳልሆኑ በተለያዩ መንገዶች ሲገልፁ ተስተውሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ