ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ቱሪስት ለማ ሐት-ትሪክ በሰራችበት ጨዋታ ጌዴኦ ዲላ ኤሌክትሪክን አሸንፏል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን አራተኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ጌዲኦ ዲላ በቱሪስት ለማ ሀትሪክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ረቷል፡፡

10:00 ሲል በጀመረው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ተከታታይ አራተኛ ድላቸውን ለማሳካት ጌዲዶ ዲላዎች ካለፈው የንግድ ባንክ ሽንፈት ለማገገም የሚረዳቸው ጨዋታ ነበር። የአሰልጣኝ መሠረት ማኔው ኤሌክትሪክን ኳስ በማንሸራሸር ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ያደረጉት ጥረት በሁነኛ አጥቂ ማጣት የተነሳ ሲባክኑ የታየበት በአንፃሩ ጌዲኦ ዲላዎች በመስመር በኩል የሚያደርጉት አስፈሪ ተሻጋሪ ኳሶች ለተበታተነው የኤሌክትሪክ ተከላካዮች ፈታኝ የነበረ ነበር፡፡

3ኛው ደቂቃ በዚህ እንቅስቃሴ የተገኘችን አጋጣሚ ቱሪስት ለማ ከመረብ አሳርፋ ጌዲኦ ዲላን መሪ አድርጋለች፡፡ ረጃጅም ኳሶች በሚገባ ያዋጣቸው እና የኤሌክትሪክ የመከላከል አደረጃጀት ሲላቸው የታዩት ዲላዎች 26ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ግብ አግብተዋል፡፡ ከቅጣት ምት መንደሪን ክንዲሁም ከርቀት ወደ ግብ ስታሻማ ቱሪስት ለማ በግንባር በመግጨት ወደ ግብ በመለወጥ ለክለቧም ሆነ ለራሷ ሁለተኛ ግብን ማስቆጠር ችላለች፡፡ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድም የረቡ ሙከራዎችን ከእንቅስቃሴ ውጪ ሳያደርጉ ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ አከታትለው የተጫዋች ቅያሪን ኤሌክትሪኮች ቢያደርጉም ከግብ ጋር ያላቸው ቁርኝት ግን እጅጉን ደካማ ነበር፡፡ ኤሌክትሪኮች በዚህኛው አገማሽ እታፈራው አድርሴ እና ጤናዬ ወመሴ ካደረጉት ሙከራ ውጪ የጠሩ ዕድሎችን ማግኘት ግን አልቻሉም፡፡ ጌዲኦ ዲላዎች አሁንም ረጃጅም ኳስን በመጣል ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ያለመታከት የደረሱ ሲሆን በእፀገነት ግርማ ካደረጉት ሙከራ በኃላ ቱሪስት ለማ ሐት-ትሪክ ሰርታ ጨዋታው በጌዲኦ ዲላ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ ለጌዲኦ ዲላ ሶስት ግቦችን ያስቆጠረችሁ ግቦችን ያስቆጠረችሁ ቱሪስት ለማ የልሳን የሴቶች ስፖርት የጨዋታ ኮከብ ተብላ ከአቶ ኢሳያስ ጅራ ሽልማቷን ተቀብላለች፡፡

ጊዜያዊ ሰንጠረዥ
# ክለብ ተጫ ልዩ ነጥብ
1 መከላከያ 4 5 10
2 ንግድ ባንክ 3 11 9
3 ኤሌክትሪክ 4 0 9
4 ሀዋሳ ከተማ 3 10 7
5 ጌዴኦ ዲላ 4 2 5
6 አቃቂ ቃሊቲ 3 -2 2
7 አአ ከተማ 4 -3 2
8 ድሬዳዋ ከተማ 3 -3 1
9 አዳማ ከተማ 3 -4 1
10 አርባምንጭ ከተማ 3 -16 0

© ሶከር ኢትዮጵያ