ሲዳማ ቡና ከ ወልቂጤ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአምስተኛው ሳምንት የመጨረሻ ቀን ላይ ሆነን የምንጠብቀው የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች።

ነጥብ ከተጋራበት ከአዳማው ጨዋታ የአራት ተጫዋቾች ለውጥ ያደራገው ሲዳማ ቡና ጉዳት የገጠመው ይገዙ ቦጋለ ፣ አምበሉ ግርማ በቀለ ፣ አበባየሁ ዮሀንስ እና አማኑኤል እንዳለን ከመጀመሪያ አሰላለፍ ውጪ አድርጓል። በምትካቸውም በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የጀመሩት ተመስገን በጅሮንድ ፣ ብርሀኑ አሻሞ እና ዮናታን ፍሰሀ እንዲሁም ዳዊት ተፈራን በቀዳሚነት ተጠቅሟል። ቡድኑ ከውጪ ዜግነት ካላቸው እና ሊጠቀምባቸው ካልቻላቸው ተጫዋቾቹ መካከልም ያስር ሙገርዋ በተጠባባቂነት ተመልሶለታል።

ባህር ዳር ላይ ድል የተቀዳጁት ወልቂጤ ከተማዎች በጨዋታው በፊት አጥቂነት ይዘዋቸው ገብተው የነበሩትን ተስፋዬ ነጋሽ እና አህመድ ሁሴንንን ወደ ተጠባባቂነት አውርደው በምትካቸው በኃይሉ ተሻገር እና አብዱርሀማን ሙባረክን ተጠቅመዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመልሳል

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
17 ዮናታን ፍሰሀ
24 ጊት ጋትኮች
2 ፈቱዲን ጀማል
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
6 ዮሴፍ ዮሃንስ
10 ዳዊት ተፈራ
15 ታመስገን በጅሮንድ
11 አዲሱ አቱላ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
9 ሥዩም ተስፋዬ
30 ቶማስ ስምረቱ
3 ረመዳን የሱፍ
25 አሚን ነስሩ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
18 በኃይሉ ተሻገር
14 አብዱልከሪም ወርቁ
13 ፍሬው ሰለሞን
20 ያሬድ ታደሰ
11 አብዱራህማን ሙባረክ


© ሶከር ኢትዮጵያ