የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 1-0 ወልቂጤ ከተማ

ከሲዳማ እና ወልቂጤ ጨዋታ መጠናቀቀ በኋላ ሱፐር ስፖርት ከቡድኖቹ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ተቀብሏል።
አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሲዳማ ቡና

ስለጨዋታው

ከሽንፈት ለመውጣት ከባድ ቡድን ነበር። እንቅስቃሴው ጥሩ ነው እንደተጨነቅነው ግን አይደለም። ዛሬ ተጫዋቾቼ ከፍተኛ መስዕዋትነት ነው የከፈሉት። በጨዋታው እያንዳንዱ ቦታ ላይ ሁሉም የሚችለውን ነው ያደረገው። ዛሬ ሦስት ነጥብ በጣም ያስፈልገን ስለነበር ብዙ ችግር የነበረው አዕምሮ ላይ ነው ፤ እሱ ላይ ነበር የሰራነው። ዞሮ ዞሮ ሦስት ነጥብ አግኝተናል መጀመሪያ ባስቆጠርነው ጎል። ጎሉንም ጠብቀን በእንቅስቃሴም ብልጫውን ወስደን አሸንፈናል።

ቡድኑ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ስለመዳከሙ

ይሄን ድካም የሚያመጣው ጎሉን ጠብቀን ለመውጣት ከሚፈጥረው ጭንቀት ነው። በመጀመሪያው 45 ያላቸውን ነገር ነው የሰጡት። ከዚያ በኃላ ያቺን ጎል ጠብቆ ለመውጣት ነው ያሰብነው እና ተሳክቶልናል።

ስለወልቂጤ

የወልቂጤን ቡድን ስላየሁት በጋራ ነው የሚነጥቁት በጋራ በህብረት ነበር የሚጫወቱት። ያንን ዕድል ነው ዛሬ የከለከልነው። የመጫወት ዕድል አላገኙም ዛሬ ክፈተት አልሰጠናቸው።

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው – ወልቂጤ ከተማ

ስለጨዋታው

ወደ ሜዳ ስንገባ ኳሱን ተቆጣጥረን በተለይ ደግሞ መሀል ሜዳ ላይ ብልጫ ወስደን የመጫወት ፍላጎት ነው የነበረን። ሲዳማዎች የነበራቸው ተነሳሽነት በጣም ደስ ይል ነበር። በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። እኛ ጋር ደግሞ ጨዋታውን እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነበሩ ተጫዋቾቻችን። ያ ከልክ ያለፈ እርግጠኝነት ሜዳ ላይ የምንፈልገውን ነገር እንዳንከውን አድርጎናል። በተለይ በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ የሚገጥሙን ነገሮች የጨዋታውን ውጤት የሚቀይሩ ውሳኔዎች ልጆቻችምን ከእንቅስቃሴ እያስወጡ ነው እና ይህን አወዳዳሪው አካል በትኩረት ቢመለከተው ደስ ይለኛል።

በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኑ ስላሳየው መነሳሳት

በእርግጥ በእንቅስቃሴ መሻሻል አለ ቡድናችን ላይ። በተለይ ሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ መረጋጋት የለም ። የምናገኛቸውን አጋጣሚዎች ለመጠቀም የመጣደፍ ነገር አለ ቡድናችን ላይ። ይህንን ለመቅረፍ በቀጣይ ጊዜያተቀብሏል።በመስራት ጥረት እናደርጋለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ